ዩኒቨርስቲው ይፋዊ የትምህርት ማስተዳደሪያ ስርዓት /eLearning Management System/ መዘርጋቱ ተነገረ

የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ትምህርትና ስነ ባህሪ ኮሌጅ ከኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጅ መማር ማስተማር ጋር በመተባበር ለመምህራን በሶስት ፣ ለተማሪዎች ለሁለት ዙር በተመረጡ አምስት ኮርሶች ላይ ሲሰጥ የነበረው የሲስተም አጠቃቀም ስልጠና ተጠናቆ ወደ ተግበር የገባ ሲሆን በስልጠናውም መሠረት የትምህርት መመዘኛ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎችን በሲስተም በመፈተን የስራዉን ውጤታማነት ለማየት ተችሏል፡፡