የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባጠቃላይ 11226 ተማሪዎችን በደማቅ ሆኔታ አስመርቀ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በቅድመ ምረቃ 7573፣ በድህረ ምረቃ 3653 ባጠቃላይ 11226 ተማሪዎችን  በዩኒቨርሲቲው ስፖርት አካዳሚ በደማቅ ሆኔታ አስመርቋል፡፡ በምርቃ ስነ-ስርዓቱ የጤና ልማትና ጸረ ወባ ማህበር መስራችና ተቀዳሚ ዳይሬክተር ለአቶ አበረ ምህረቴ እንዲሁም በኮርኔል ዩኒቨርሲቲ በስነሕይወትና ከባቢያዊ ምህንድስና አለማቀፍ ፕሮፌሰርና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተመራማሪ ለሆኑት ለፕሮፌሰር ታም ስቴንሁስ የክብር ዶክተሬት ሰጥቷል፡፡