የስራ ማስታወቂያ

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ በአካዳሚክስ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንትነት ፣ በአስተዳድር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንትነት ፣በቢዝነስና ልማት  ምክትል ፕሬዚዳንትነት እና በኢንፎርሚሽንና ስትራቴጂክ ኮሙኒኬሽን ምክትል ፕሬዚዳንትነት መቅጠር ይፈልጋል፡፡

የማወዳደሪያ መሰፈርት

1ኛ. የትምህርት ደረጃ የሁለተኛ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት

2ኛ.በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ሀላፊነት  እርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከተ/ች፣

3ኛ.በሚያመለክቱበት  ዘርፉ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርትን ተደራሽነት፣ፍትሃዊነት፣ ጥራትን ተገቢነትና ዓለም አቀፋዊነት ለማሳካት፣ ተቋማቱን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት  አስተዋጽለማበርከት   የሚያስችል ስተራቲጅካዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል

4ኛ.የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ተወካዮች፣ የሰኔት አባላትናሌሎች የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለፃ መስጠት የሚችል/የምትችል

 

አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በመገናኛ ብዙሀን ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያለበለጠ ስትራቴጅክ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኢንቮሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ  ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ወይም አዲስ አበባ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ግንኙነት ጽ/ቤት ድረስ ማሰገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች 09 18 78 22 97 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል

 

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ

Friday, April 27, 2018 - 01