የሳይንስ ኮሌጅ የማህበረተሰብ አገልግሎት

 

                        ሳይንስ ኮሌጅ ዓርአያነቱ እንደቀጠለ ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ኮሌጅ መምህራንና ተማሪዎች በከተማዋ ዓርአያነት ያለው የማህበረተሰብ አገልግሎት  አከናወኑ፡፡

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ “አንድ ቀን ለህዝቤ” በሚል መሪ ቃል በሚያከናውነው ወርሃዊ የቅዳሜ የማህበረተሰብ አገልግሎት ንቅናቄ የሳይንስ ኮሌጅ  መምህራንና ተማሪዎች ከኬምስትሪ ትምህርት ክፍል ውጪ   በከተማው ቤዛዊት (በቀድሞው ቤተመንግስት) ተብሎ በሚታወቀው  አካባቢ በመንቀሳቀስ የጽዳት ዘመቻ አካሂደዋል፡፡

ይህንን በጎ ተግባር በኮሌጅ ደረጃ ያስተባበሩት የሳይንስ ኮሌጅ የድህረ- ምረቃ፣ ምርምርና ማህበረተሰብ አገልግሎት ምክትል ዲን ዶ/ር ነጋ ጣሴ የኮሌጁ ማህበረተሰብ ወሩን ጠብቆ በተደራጀ መልኩ በቋሚነት የማህበረተሰብ አገልግሎት ስራዎችን እንደሚሰሩ ጠቅሰው፤ ዩኒቨርሲቲው በራሱ ለህብረተሰቡ አርአያ የሚሆኑ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅም እምነታቸውን ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ነጋ አክለውም  አካባቢን በማፅዳት ረገድም ግንባር ቀደም በመሆን በህብረተሰቡ ዘንድ እንደባህል እስኪቆጠር ድረስ ስራው በቀጣይነት እንደሚከናወን እምነታቸውን አንፀባርቀዋል፡፡

በዚህ የኮሌጁ በጎ የሆነ የማህብረተሰብ ተኮር ንቅናቄ 27 መምህራንና 270 ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡