ክፍት የውስጥ የኃላፊነት የስራ ማስታወቂያ (ሳይንስ ኮሌጅ)

ቀን፡ 23/12/2011 ዓ.ም
ክፍት የውስጥ የኃላፊነት የስራ ማስታወቂያ 
========================
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች መመደቢያ መመሪያ መሰረት ብቁ አመልካቾችን ከዩኒቨርሰቲው አወዳድሮ ለሳይንስ ኮሌጅ የድህረ ምረቃ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ዲን መቅጠር ይፈልጋል፡፡

የማወዳደሪያ መስፈርት
1ኛ. የትምህርት ደረጃ፡ ሌክቸረርና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት

2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት ዕርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች፤

3ኛ. በሚያመለክቱበት አካዳሚክ ክፍልና ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትኃዊነት፣ ጥራት፣ ተገቢነትና ዓለምአቀፋዊነትን ለማሳካት፣ አካዳሚክ ክፍሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለማቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/ምትችል፤

4ኛ. የአካዳሚክ ክፍሉ ማህበረሰብ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለጻ መስጠት የሚችል/ምትችል፤

አመልካቾች፡-
ይህ ማስታወቂያ በዩኒቨርሰቲው የማስታወቂያ ሰሌዳና ድህረ-ገጽ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች +251 58 3206097/99/+ 251 918 35 3494 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል