ማስታወቂያ

ታህሳስ 24/2011 ዓ.ም

ማስታወቂያ

 

ለሚመለከታችሁ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች

በቅርቡ በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈጥረው በነበሩ አለመረጋጋቶች ምክንያት በዩኒቨርሰቲያችን አንዳንድ ግቢዎች ትምህርት ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም በሌሎች ግቢዎች የመማር ማስተማሩ ሂደት ያለምንም ችግር አሁንም እንደቀጠለ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ይህንን ተከትሎ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ዛሬ ታህሳስ 24/2011 ዓ.ም በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ተወያይቶ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ወስኗል፡፡

በመሆኑም ተማሪዎች ጥር 1 እና 2/2011 ዓ.ም በትምህርት ገበታችሁ ላይ ተገኝታችሁ ትምህርታችሁን እንድትቀጥሉ ዩኒቨርሰቲው ጥሪ አስተላልፏል፡፡

 

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

Thursday, January 3, 2019 - 07