ማስታወቂያ

     የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ለቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች በላከዉ የአመራር እና አስራር ነፃነት  መመሪያ (IOT’s Autonomos Directive 001/2013) መሰረት እንዲሁም ለኢትዮጲያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መሪዎች ማወዳደሪያ መስፈርት በወጣው መመረያ ላይ በመመስረት  በባሕር ዳር ዩንቨርስቲ ለባሕርዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንትፊክ ዳይሬክተርነት እና ለኢትዮጲያ ቴክስታይል እና ፋሽን ዲዛይን ኢንስቲትዩት ሳይንትፊክ ዳይሬክተርነት የሃለፊነት ቦታ ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡

የማወዳደሪያ መሰፈርት

  1ኛ. የትምህርት ማእረግ ፡- ረዳት ፕሮፌሰር እና ከዚያ  በላይ ያለው/ያላት

 

2ኛ. የትምህርት ደረጃ፡- ሶስተኛ ዲግሪ / የሁለተኛ ዲግሪ በ ኢንጅነሪንግ እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያለው/ያላት

3ኛ. የስራ ልምድ ፡-2 ዓመት  ለሶስተኛ ዲግሪ / 5 ዓመት ለሁለተኛ ዲግሪ     በከፍተኛ ትምህርት ተቋም በከፍተኛ አመራርነት ከ ትምህርት ክፍል ሀላፊነት በላይ ያገለገለ/ ያገለገለች

4ኛ.በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ሀላፊነት  እርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከተ/ች፣

5ኛ.በሚያመለክቱበት  ዘርፉ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርትን ተደራሽነት፣ፍትሃዊነት፣ ጥራትን ተገቢነትና ዓለም አቀፋዊነት ለማሳካት፣ ተቋማቱን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት  አስተዋጽኦ ለማበርከት   የሚያስችል ስተራቲጅካዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል

6ኛ.የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ተወካዮች፣ የሰኔት አባላትናሌሎች የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለፃ መስጠት የሚችል/የምትችል

 

አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በመገናኛ ብዙሀን ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያለበለጠ ስትራቴጅክ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኢንቮሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ  ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ወይም አዲስ አበባ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ግንኙነት ጽ/ቤት ድረስ ማሰገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች 09 18 78 22 97/09 18 35 34 94  ደውሎ ማነጋገር ይቻላል

የዩኒቨርሲቲውን ድረ ገጽ www.bdu.edu.et መመልከት ይቻላል

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ