የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች የኮቪድ 19 ክትባት ዘመቻን አስጀመሩ።

(ሰኔ 11፣2014 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር)፦ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች የኮቪድ 19 ክትባት ዘመቻን በዛሬዉ እለት በጥበበ ግን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስጀምረዋል።

በዘመቻዉ የኮሌጁ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፕሮፌሰር የሽጌታ ገላዉን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ራሳቸዉ መጀመሪያ በመከተብ ለሌሎች አሳይተዋል።

የኮቪድ-19 ክትባት የሚሰጠዉ ከ 12 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆናቸው ሰዎች ሲሆን በሽታ መከላከያ ክትባቱ በሽታ የመከላከል አቅማችዉን በማጎልበት ከህመምና ሞት ይታደጋል። በዚዉ ልክ ለሌሎች ሰዎችም እንዳያስተላልፉ ይከላከላል፡፡

ሌሎች የኮሌጁ መምህራን፣ ሰራተኞችና ተማሪዎች የከፍተኛ አመራችን አርያ ተከትለዉ የኮቪድ 19 ክትባት ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የክትባት ዘመቻው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኔ 13 የሚቆይ ይሆናል።

#Dedicated to #excellence #committed to #care!!!

Follow us cmhsbd
Facebook: https://www.facebook.com/cmhsbdu/
Website: http://www.bdu.edu.et/cmhs/
Telegram: https://t.me/Information-office-CMHS-BDU

date: 
Saturday, June 18, 2022 - 07:30

Contact CMHS

College Of Medicine and Health Sciences

Bahir Dar University

 Bahir Dar, Ethiopia

Phone:- +251-0582-9 99275

P.o.box:- 79

e-mail:- collegehealthscience@gmail.com

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University