Operation Eye sight Universal-Canada (OES) and Partners in Education Ethiopia በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዓይን ህክምና ክፍል ድጋፋዊ ጉብኝት አደረገ፡፡

(የካቲት 16፣2014 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር)፦ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ /ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዓይነ-ስዉርነትን ለመከላከልና የአይን እይታን ለመመለስ ከሚሰሩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች Operation Eye sight Universal (OES) and Partners in Education Ethiopia ጋር በመተባበር በጥበበ ግዮን ስፔሻልዝድ ሆስፒታል የዓይን ህክምና ክፍል የሚሰጠውን አገልግሎት በድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ተጎበኘ፡፡

OEU ለሆስፒታሉ ቀደም ብሎ ባደረገው ድጋፍ የዓይን ሕክምናክፍል በማቋቋም መደበኛ የዓይን ሕክምና አገልግሎት ለአካባቢዉ ማሕበረሰብ መስጠት እንዲቻል ማድረጉ በሕክምና መሳሪያዎች እጥረት ምክኒያት ሲከሰት የነበረዉን ተግዳሮትም በእጅጉ አሻሽሎታል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት የዓይን ሕክምና አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ ዘመናዊና ደረጃቸዉን የጠበቁ ቁሳቁሶች ለግሰው የዓይን ህክምና አገልግሎት እንዲሰጥ በማስቻላቸው ለለጋሽ ድርጅቶችና ከፍተኛ አመራሮች የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ/ ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር ፕ/ር የሺጌታ ገላው አመሰግነዋል:: በጉብኝቱ ወቅት ኮሌጁ ከለጋሽ ድርጅቶች ጋር ከ4 ዓመት በፊት ስምምነት በማድረግ በክልላችን የዐይን ሕክምና አገልግሎቱን ለማሻሻል ስራዎች ታቅደው እየተሰሩ እንደሆነ ዋና ሥራ አስፈፃሚገልጸዋል፡፡

ፕሮፌሰሩ አክለዉም ድርጅቶች በቀጣይ ማድረግ ስላለባቸው ዋና ዋና ድጋፎች ለሀላፊዎች ገልፀዋል:: በውውይቱም በቀጣይ ተጨማሪ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች ድጋፍ : ለዓይን ቀዶ ህክምና የሚያስፈልጉ መድኃኒቶችና ቁሳቁሶች ድጋፍ: በትብብር በደበኛ የመስክ የዓይን ህክምና (Regular Outreach Program) በተመረጡ ሆስፒታሎች ስለመጀመር: በህንድና ሌሎች የዉጭ ሀገራት ለዓይን ሐኪሞች የድህረ ስፔሻሊቲ (Subspeciality) ስልጠና ስለማመቻቸት: ራሱን የቻለ ሞዴል የሚሆን የዓይን ህክምና ማዕከል በጥበበ ግዮን ስለመገንባት: በትምህርት ቤቶች የዓይን ምርመራ በማድረግ የዕይታ መነፅር ስለማቅረብ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ መግባባት የተደረሰ ሲሆን እነዚህ ጉዳዮች እየተዘጋጃ ባለው የጋራ የአምስት ዓመት ስልታዊ እቅድ ዉስጥ ተካተው የሚሰራ ይሆናል::

በጉብኝቱ ወቅት የተገኙት የ 'Operation Eye sight Universal (OES)' ድርጅት ፕሮግራም ኃላፊ ዶ/ር ቦቴንግ ዊያፈ እና የ'Partners in Education Ethiopia' ዳይሬክተር አቶ ይሃለም አበበ በበኩላቸዉ የተቀናጀና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ በማድረግ የዓይን ህክምና ክፍሉን በመሳሪያ: በሰው ኃይልና በአሰራር ለማላቅ እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል:: ሆስፒታሉ ዓይን ክፍሉ ያለበትን የቀዶ ጥገና ክፍል እጥረት አማራጮችን በመፈለግ በቶሎ መፍታት እንደሚገባ ተናግረዋል::

Operation Eye sight Universal-Canada (OES) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ/ ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2013 ዓ.ም የዓመቱ ምርጥ አጋር በመሆን ያሸነፈ መሆኑ የሚታወስ ነዉ፡፡

date: 
Thursday, February 24, 2022 - 05:15

Contact CMHS

College Of Medicine and Health Sciences

Bahir Dar University

 Bahir Dar, Ethiopia

Phone:- +251-0582-9 99275

P.o.box:- 79

e-mail:- collegehealthscience@gmail.com

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University