Children Surgery International

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጋባዥነት በአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት ከሚገኘው ችልድረን ሴሪጀሪ ኢንተርናሽናል /Children Surgery International/ የህክምና ማዕከል በመጡ 18 የህክምና ዶክተሮች እና የጤና ባለሙያዎች የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ/Cleft Leap and Cleft Palate/ ችግር ላለባቸው እንዲሁም ከአንገት ባለይ በጀሮ አካባቢ ለሚፈጠሩ ዕጢዎች የቀዶ ጥገና አገልግሎት በፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል እየተሰጠ ይገኛል፡፡አገልግሎቱ ዛሬ የተጀመረ ሲሆን እስከ ጥቅምት 24፣ 2010 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል፡፡

በሀገራችን የላንቃና የከንፈር መሰንጠቅ ችግር ያለባቸው ዜጎች ቁጥር ቀላል የማይባል መሆኑን የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአካዳሚክ እና ምርምር ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ፈንታሁን ቢያድግልኝ ገልፀው ችግሩን ለማቃለል የአምስት ቀኑ ህክምና ክፍተኛ አስተዋፆ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡ ህክምናው ዩኒቨርሲቲው ከሚያከናውናቸው የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራ አንዱ አካል መሆኑንም ዶ/ር ፈንታሁን አያይዘው ገልፀዋል፡፡

በህክምናው 40 እና ከዚያ በላይ የሚሆኑ ዜጎችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እደሚሆኑ ታውቋል፡፡

 
Date: 
Tuesday, January 1, 2019 - 12:00
place: 
Bahir Dar University
images: 

Contact CMHS

College Of Medicine and Health Sciences

Bahir Dar University

 Bahir Dar, Ethiopia

Phone:- +251-0582-9 99275

P.o.box:- 79

e-mail:- collegehealthscience@gmail.com

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University