ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ርቀትና ተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም የአዲስ ተማሪዎች ቅበላ መስፈርት
እዉቅና ባላቸዉ ፕሮግራሞች የት/ት ሚኒስቴርን እና የዩኒቨርስቲዉን የቅበላ መስፈርቶች/መመሪያዎች በተከተለ መልኩ የተማሪዎች ቅበላ ተደርጎ ጥራት ያለዉ ትምህርት ይሰጣል፡፡
አጠቃላይ መመሪያዎች፡-
ለቅድመ ምረቃ
- የብቃት ሰርተፊኬት ለሚያስፈልጋቸው የትምህርት ክፍሎች የብቃት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
- የብቃት ሰርተፊኬት ለማያስፈልጋቸው 2 ዓመት የሥራልምድ
- በቀድሞው 12 ክፍል መመዝገብ አይቻልም
ለድህረምረቃ
- የመጀመሪያ ዲግሪ ኦርጂናል ማስረጃና ሁለት ፎቶኮፒ
- ኦፊሺያል ትራንስክርቢት ከምዝገባ በፊት ቀድሞ መድረስ አለበት፡፡
ማሳሰቢያ
- የት/ትፕሮግራሞችን እና መግቢያ መስፈርቶችን በተመለከተ ማንኛዉም ጥያቄ ካለዎት የተከታታይ እና ርቀት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሰራተኞችን እንዲሁም የዩኒቨርስቲዉን ሬጅስትራር ባለሞያዎች ያማክሩ፡፡