የመጀመርያ እርዳታ አሰጣት ስልጠና ለተማሪዎች ተሰጠ

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲዉ የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ከጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጤና ባለሙያ የሆኑትን አቶ ሰሎሞን እምሻዉና አቶ ይሁን ምስክርን በማስመጣት ከዩኒቨርሲቲዉ ለተመለመሉ ወ 17 ሴ 4 ድምር 21 ተማሪዎች ከ 10-11/09/2011 ዓ/ም ድረስ የመጀመርያ እርዳታ አሰጣት ስልጠና እንዲወስዱ በማድረግ ተማሪዎች ሌሎችን ለማገዝ የሚበቃቸዉን ስልጠና በባለሙያዎች በበቂ ሆኔታ ሰልጥነዋል ፡ በስልጠናዉ ወቅትም በቲወሪ የተማሩትን በተግባር ልምምድ አድርገዉ በቂ ዕዉቀት አግኝተዉ ሌሎችን ለማገዝ ዝግጁ እንደሆኑ አንዳንድ ሰልጣኞች ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም ስልጠናዉን ላጠናቀቁ 21 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲዉ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት አስተዳደር ኤክስኪቲቨ ዳይሬክተር ከሆኑት ከዶ/ር ደሳለኝ እጅጉ እጅ ሰርተፍኬት ተቀብለዉ የስራ መመርያም ጭምር በማስተላለፍ ስልጠናዉ ተጠናቋል፡፡