ለፔዳ ግቢና ለቢዝነስና ኢኮኖሚክሰ ኮሌጅ አስተዳደር ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ከፔዳ ግቢ ማኔጅንግ ዳይሬክተርና ከቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ማኔጅንግ ዳይሬክተር ጋር በመተባበር በሁለቱም ግቢዎች በተዘጋጀዉ አዳራሽ ላይ በደንበኞች አያያዝና ስነምግባር ዙርያ ከቢዚነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በመጡ አሰልጣኞች ከ23-24/11/2011 ዓ/ም ድረስ ለ 110 ሰልጣኞች ስልጠና ተሰጧቸዋል፡፡ በዚህም ስልጠና ተሳታፊዎች ከስልጠናዉ ሰፊ ዕዉቀት እንዳገኙና ራሳችንንም እንድንፈትሽና እንድናይ ያደረገን በመሆኑ ለቀጣይ ስራችን ከፍተኛ መነሳሳትን ፈጥሮልናል ፡ነገር ግን በዚህ ስልጠና ላይ ሁሉም የዩንቨርሲቲዉ ማህበረሰብ በተለይ የበላይ አመራሮች ስልጠናዉን ቢወስዱ የተሸለ ስራ ይሰራል ብለን እናምናለን በማለት ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲዉ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሆኑት አቶ ወርቁ አበበ ይህ ስልጠና ለእናንተ ብቻ ሳይሆን ለዩኒቨርሲቲዉ ለሁሉም ማህበረሰብ በተከታታይነት የሚሰጥ ይሆናል ፡፡ ስለሆነም እናንተም በሰለጠናችሁበት አግባብ የደንበኛን ክቡርነት በመገንዘብ ከስልጠናዉ በቀሰማችሁት ዕዉቀት መሰረት የአገልጋይነት ወኔን በመላበስ ተግታችሁ እንድትሰሩ እያሳሰብኩ ቀጣይም ወደ ስራ ክፍላችሁ ዳይሬክቶሬቱ በመንቀሳቀስ የስልጠናዉን አፈጻጸም የሚከታተል መሆኑን በመግለጽ ስልጠናዉ ተጠናቋል፡፡