ለተመራቂ ተማሪዎች SPSS ስልጠና ተሰጠ

የባህርዳ ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት በፔዳ ግቢ የሁለተኛ ዲግሪ ለሚማሩ ወ 41 ሴ 7 ድ 48 የሶሻል ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎች SPSS ስልጠና ከ 12-16/09/2011 ዓ/ም ለተከታታይ 5 ቀናት ከስታትስቲክስ ትምህርት ክፍል በመጡ ሁለት አሰልጣኞች ማለትም አቶ ተሸገር አሰፋና ወ/ሮ እየሩስ አስማረ አማካኝነት ስልጠናዉን በብቃት ሰልጥነዋል ፤ ሰልጣኞችም ከስልጠናዉ በቂ ዕዉቀት እንዳገኙና ቀጣይ ለሚመረቁበት የመመረቅያ ጽሁፋቸዉንም በተገቢዉ መንገድ ለመግለጽና ለመተንተን የሚረዳቸዉን ዕዉቀት እንዳገኙ ገልጸዋል ፡፡ በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲዉ የአጠቃላይ ጥራት አስተዳደር ኤክስኪቲቨ ዳይሬክተር ከሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ እጅጉ እጅ ሰርተፍኬት ተቀብለዉ ስልጠናዉ ተጠናቋል፡፡