ለሴት ተማሪዎች የሜንተር ሺፕ ስልጠና ተሰጠ

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲዉ የስርዓተጾታ ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባባር ከ7ቱም ግቢዎች ለተወጣጡ 38 ሴት ተማሪዎች አቻ ሴት ተማሪዎችን በመማር ማስተማሩና በአጠቃላይ በህይወታቸዉ ዙርያ እንደ ታላቅ እህት ሆነዉ እንዲያማክሩ በማሰብ ከ 12-13/08/2011 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ከትምህርትና ስነባህሪ ትምህርት ኮሌጅ በመጡ በመምህር አስራት ደርብ አማካኝነት በበቂ ሁኔታ ስልጠናዉ ተሰጧል ፡፡
ከስልጠናዉ በኃላም የዩኒቨርሲቲዉ የስልጠና ዳይሬክቶሬት የሆኑት አቶ ወርቁ አበበ ለተማሪዎች በቀጣይ ስራቸዉ ዙርያ ተጠናክረዉና ተበራተዉ እንደታላቅ እህት ራሳቸዉን በመቁጠር በሰለጠኑት አግባብ ስራቸዉን እንዲያከናዉኑ ከአደራ ጭምር ጋር በማሰብ እንዲሰሩ በማለት አስተያየታቸዉን በመስጠት ስልጠናዉ ተጠናቋል፡፡