ለጸጥታና ደህንነት ሰራተኞችና ለፕሮክተሮች ስልጠና ተሰጠ

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲዉ ጸጥታና ደህንነት ዳይሬክቶሬትና ተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር 80 ለሚሆኑ የጸጥታ ሰራተኞችና ፕሮክተሮች ከቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ከመጡ አሰልጣኞች አማካኝነት በደንበኞች አያያዝ ዙርያ አሁን እየተሰራ ካለዉ ነባራዊ ሁኔታና ቀጣይ በምን መልኩ ደንበኛን ማገልግል እንዳለባቸዉ በባለሙያዎች ከ4—7/10/2011 ለ4 ቀን በሁለት ዙር ስልጠና ተሰጧቸዋል፡፡ሰልጣኞችም ከሰልጠናዉ በቂ ዕዉቀት እንዳገኙና ቀጣይም ከዚህ በተሸለ መንገድ በሰለጠንነዉ አግባብ ደንበኞችን እንደምናረካ እርግጠኞች ነን በማለት አስተያየታቸዉን በመስጠት ስልጠናዉ ተጠናቋል፡፡

ለአብያተ መጽሃፍት አስተባባሪዎች ስልጠና ተሰጠ

የባህርዳ ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲዉ አብያተ መጽሃፍት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር General Concept of Library Automation System እና የኮሃ አዉቶሜሽን አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ ከዩኒቨርሲቲዉ የ አይ.ሲ.ቲ. ዳይሬክቶሬት በመጡ ባለሙያዎች አማካኝት ስልጠና ተሰጧል፡፡ ሰልጣኞችም በሰለጠኑት አግባብ ስራዎች በምን ደረጃ ላይ እንዳሉ ለማየትና ለመገምገም ያመቻቸዉ ዘንድ በጋራ በመሆን የሁሉንም ግቢዎች አብያተ መጽሃፍቶችን በመጎብኘት የሰለጠኑትን በተግባር የማሳየት ስራ ተሰርቷል፡፡

ለጤና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ

የባህርዳ ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲዉ የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ከህክምናና ጤና ሳይን ኮሌጅ በመጡ ባለሙያዎች ከሁሉም ግቢዎች ለተወጣጡ ነርሶችና የጤና መኮንኖች Integrated Emergency Patient Training በሚል ርዕስ ዙርያ ለ 30 የህክምና ባለሙያዎች ከ 27—30/09/2011 ዓ/ም ድረስ ለ4 ተከታታይ ቀናት ስልጠና ተሰጧቸዋል፡፡ ሰልጣኞችም ከስልጠናዉ በቂ ዕዉቀት እንዳገኙና ቀጣይም ተመሳሳይ መድረኮች ተፈጥረዉ የተለያዩ ስልጠናዎች እንዲሰጣቸዉ አሳስበዋል ፡፡በመጨረሻም ሥልጠናዉን ላጠናቀቁ የጤና ባለሙያዎች የዩኒቨርሲቲዉ አጠቃላይ ጥራት አስተዳደር ኤክስኪቲቭ ዳይሬክተር ከሆኑት ከ ዶ/ር ደሳለኝ እጅጉ እጅ ሰርተፍኬት ተቀብለዋል የስራ መመርያም ተሰጧቸዋል፡፡

ለተመራቂ ተማሪዎች የስራ ተኮር የምክር አገልግሎት ስልጠና ተሰጠ

የባህርዳ ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲዉ የዉጤታማ ትግበራ ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር በዩኒቨርሲቲዉ ለሚገኙ የ 2011 ዓ/ም የመጀመርያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎች ከትምህርትና ስነባህሪ ትምህርት ኮሌጅ በመጡ አሰልጣኞች የስራ ተኮር የምክር አገልግሎት ስልጠና ተሰጧቸዋል ፡፡
በዚህም የስልጠና ወቅት ተመራቂ ተማሪዎች ከተመረቁ በኃላ እንዴት ስራን እንደሚፈልጉና እንዴት ወደስራ ዓለም እንደሚገቡ ግንዛቤ የተፈጠራላቸዉ ሲሆን በስልጠናዉ ማጠቃለያ ላይም ዩኒቨርስቲያችን ተማሪዎችን አስመርቆ መልቀቅ ብቻ ሳይሆን እንዴት ወደ ስራ ዓለም እንደሚገቡም ጭምር ግንዛቤ እየፈጠረ የሚከታተል በመሆኑ ሰልጣኞች በተሰጣችሁ ግንዛቤ መሰረት ዉጤታማ እንድትሆኑ በማለት የዩኒቨርሲቲዉ የስልጠና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ወርቁ አበበ ተማሪዎችን አሳስበዋል፡፡

ለተመራቂ ተማሪዎች SPSS ስልጠና ተሰጠ

የባህርዳ ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት በፔዳ ግቢ የሁለተኛ ዲግሪ ለሚማሩ ወ 41 ሴ 7 ድ 48 የሶሻል ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎች SPSS ስልጠና ከ 12-16/09/2011 ዓ/ም ለተከታታይ 5 ቀናት ከስታትስቲክስ ትምህርት ክፍል በመጡ ሁለት አሰልጣኞች ማለትም አቶ ተሸገር አሰፋና ወ/ሮ እየሩስ አስማረ አማካኝነት ስልጠናዉን በብቃት ሰልጥነዋል ፤ ሰልጣኞችም ከስልጠናዉ በቂ ዕዉቀት እንዳገኙና ቀጣይ ለሚመረቁበት የመመረቅያ ጽሁፋቸዉንም በተገቢዉ መንገድ ለመግለጽና ለመተንተን የሚረዳቸዉን ዕዉቀት እንዳገኙ ገልጸዋል ፡፡ በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲዉ የአጠቃላይ ጥራት አስተዳደር ኤክስኪቲቨ ዳይሬክተር ከሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ እጅጉ እጅ ሰርተፍኬት ተቀብለዉ ስልጠናዉ ተጠናቋል፡፡

የመጀመርያ እርዳታ አሰጣት ስልጠና ለተማሪዎች ተሰጠ

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲዉ የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ከጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጤና ባለሙያ የሆኑትን አቶ ሰሎሞን እምሻዉና አቶ ይሁን ምስክርን በማስመጣት ከዩኒቨርሲቲዉ ለተመለመሉ ወ 17 ሴ 4 ድምር 21 ተማሪዎች ከ 10-11/09/2011 ዓ/ም ድረስ የመጀመርያ እርዳታ አሰጣት ስልጠና እንዲወስዱ በማድረግ ተማሪዎች ሌሎችን ለማገዝ የሚበቃቸዉን ስልጠና በባለሙያዎች በበቂ ሆኔታ ሰልጥነዋል ፡ በስልጠናዉ ወቅትም በቲወሪ የተማሩትን በተግባር ልምምድ አድርገዉ በቂ ዕዉቀት አግኝተዉ ሌሎችን ለማገዝ ዝግጁ እንደሆኑ አንዳንድ ሰልጣኞች ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም ስልጠናዉን ላጠናቀቁ 21 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲዉ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት አስተዳደር ኤክስኪቲቨ ዳይሬክተር ከሆኑት ከዶ/ር ደሳለኝ እጅጉ እጅ ሰርተፍኬት ተቀብለዉ የስራ መመርያም ጭምር በማስተላለፍ ስልጠናዉ ተጠናቋል፡፡

ለሴት ተማሪዎች የሜንተር ሺፕ ስልጠና ተሰጠ

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲዉ የስርዓተጾታ ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባባር ከ7ቱም ግቢዎች ለተወጣጡ 38 ሴት ተማሪዎች አቻ ሴት ተማሪዎችን በመማር ማስተማሩና በአጠቃላይ በህይወታቸዉ ዙርያ እንደ ታላቅ እህት ሆነዉ እንዲያማክሩ በማሰብ ከ 12-13/08/2011 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ከትምህርትና ስነባህሪ ትምህርት ኮሌጅ በመጡ በመምህር አስራት ደርብ አማካኝነት በበቂ ሁኔታ ስልጠናዉ ተሰጧል ፡፡
ከስልጠናዉ በኃላም የዩኒቨርሲቲዉ የስልጠና ዳይሬክቶሬት የሆኑት አቶ ወርቁ አበበ ለተማሪዎች በቀጣይ ስራቸዉ ዙርያ ተጠናክረዉና ተበራተዉ እንደታላቅ እህት ራሳቸዉን በመቁጠር በሰለጠኑት አግባብ ስራቸዉን እንዲያከናዉኑ ከአደራ ጭምር ጋር በማሰብ እንዲሰሩ በማለት አስተያየታቸዉን በመስጠት ስልጠናዉ ተጠናቋል፡፡

A Website of the Center for Capacity Building Programs Finally Up!

With the committed cooperation and follow up of the University's ICT Directorate, a website is now constructed for easy communication of the Center's activities, plans, and reports of all aspects of its capacity building tasks. Ato Birhanu and Ato Yibletal from the Teaching and Learning Technology Division of the Directorate took the primary responsibility in building the website, and the Center appreciates all their efforts! 

First Attempt to Compile Faculty Directory Came to Fruition

The Center for Capacity Building Programs releases a faculty directory consisting of the basic profile of about 300 faculty members of Bahir Dar University. A faculty information collection form was dispatched in 2008 E.C. asking each faculty members' educational background, teaching experience, publication history, research interest, and contact information. An elecctronic version of a "yelow page" of the faculty members who submitted their information was prepared this year. The information is meant to be used by anyone in the campus.

Training given for more than 40 Doctoral Students and Staff

Two rounds of a three-day intensive training on Qualitative Research Methods was organized and conducted by the Center from June 06-08 and 14-16, 2017. The training was delivered by Dr. Meskerem Lechissa. Topics and practical activities included: the different types of qualitative research, construction and use of qualitative data gathering tools, qualitative data analysis, and use of software in qualitative data analysis process.

Subscribe to Center for Capacity Building Programs RSS