አቋማተ 5ኛውን ሀገር አቀፍ የአማርኛ ቋንቋ እና የባሕል ዘርፎች ዓውደ ጥናት አካሄደ

 
የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም ፭ኛውን ሀገር አቀፍ የአማርኛ ቋንቋና የባሕል ዘርፎች ዓውደ ጥናት ሚያዝያ ፳፰ እና ፳፱ ፳፻፱ ዓ.ም በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ትልቁ አዳራሽ አካሄደ፡፡
መርሃግብሩ በተቋሙ ዳይሬክተር አቶ መለሰ ገላነህ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ተከፍቷል፡፡ አቶ መለሰ እንዳሉት አቋማተ የአማርኛ ቋንቋንየመግለጽደረጃበማሳደግየሳይንስናቴክኖሎጂእንዲሁምየምርምርናጥናትቋንቋለማድረግእየተጋ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የእለቱ የክብር እንግዳና የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኂሩት ካሳው ንግግር አድርገዋል፡፡ ዶ/ር ኂሩት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በአማርኛ ቋንቋ መበልጸግ ላይ እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀው የአብክመባህልናቱሪዝምቢሮከሚመለከተውከትምህርትቢሮጋርበመሆን የሚጠበቅበትን ድርሻ እደሚወጣ ተናግረዋል፡፡
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አማርኛ ቋንቋን ማበልፀግና ማሳደግ ለሀገር ልማት ያለውን ፋይዳ ቀድሞ በመረዳት እየሰራ መሆኑን በመርሃግብሩ ላይ ተሳታፊ የነበሩት የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙሉነሽ አበበ ገልፀዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ በአማርኛ ቋንቋ ዙሪያ የተሰሩ በርካታ የምርምር ጽሁፎች ቀርበው በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች፣ መምህራንና ጥሪ በተደረገላቸው እንግዶች ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡
 
 
 
 
 

Share