፭ኛው ሀገር አቀፍ የአማርኛ ቋንቋና የባሕል ዘርፎች ዓውደ ጥናት ነገ ሚያዝያ ፳፰ ፳፻፱ ዓ.ም ይጀምራል

የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም ፭ኛውን ሀገር አቀፍ የአማርኛ ቋንቋና የባሕል ዘርፎች ዓውደ ጥናት ሚያዝያ ፳፰ እና ፳፱ ፳፻፱ ዓ.ም በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ትልቁ አዳራሽ ያካሂዳል፡፡
በመርሃ ግብሩ በአማርኛ ቋንቋ ዙሪያ የተሰሩ በርካታ የምርምር ጽሁፎች ይቀርባሉ፤ ውይይትም ይካሄዳል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች፣ መምህራንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይካሄዳል፡፡ 
 
ተቋሙ መላው የዩኒቨርሲቲው መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በመርሀ ግብሩ እንዲታደሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡

Share