የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ፩ኛ ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ጉባኤ

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር
፩ኛ ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ጉባኤ
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በሚያዚያ ወር ፳፻፱ ዓ.ም. የሴክተሩን የመጀመሪያ ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ጉባኤ “የባህልና ቱሪዝም ሃብቶች ልማት ለሀገራዊ ዕድገት” በሚል ርዕስ ያካሂዳል፡፡ በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩ አጥኝዎች፣ ተመራማሪዎች፣ መምህራን፣ አማካሪዎች እና ፖሊሲ አውጭዎች በሚከተሉት ዝርዝር የጥናት ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የጥናት ጽሑፎቻቸውን አጽሕሮት እንዲያቀርቡ ይጋበዛሉ፡፡
ለቱሪዝም መዳረሻዎች ልማት  ምቹ ሁኔታዎችና ተግዳሮቶች በኢትዮጵያ፣ 
የቱሪዝም የማስተዋወቅ ስራን የመምራት፣ የማደራጀት እና ውጤታማ የማድረግ ስልቶች፣
የቱሪዝም አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፣ 
ባህላዊ ኩነቶችን እና ባህላዊ የእምነት ስርዓቶችን ወደ ቱሪዝም ገበያው ማስገባት ለሃገራዊ ልማት ያለው አስተዋጽኦ፣ 
የፓርኮች ደህንነትና ልማት በኢትዮጵያ ፣
ለባህል ሙያ ተቋማት የደረጃ ምደባ አስፈላጊነት እና ነባራዊ ሁኔታዎች ዳሰሳ ጥናት፤
ለተለያዩ አገራዊ የባህል ምርቶች መለያ (brand) መስጠትና አስፈላጊነቱ፤
በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ እስካሁን የተጠኑ ጥናቶች ውጤትና ተደራሽነት ዳሰሳ ጥናት፣ 
የሃገራችን ኢትዮጵያ የባህላዊ ቱሪዝም አቅም እና ምቹ ሁኔታ፤
ማሳሰቢያ፡ በውድድሩ የተመረጡ የጥናት ጽሑፎች ለኅትመት የሚበቁና በሚዘጋጀው የጥናትና ምርምር ጉባዔ ላይ የሚቀርቡ ሆኖ አሸናፊዎች የማበረታቻ ክፍያ ይኖራቸዋል፡፡
የጥናት ጽሑፎችን ለመለየትና አሸኛፊዎችን ለመምረጥ የሚከተሉት ጉዳዮች ከግምት ውስጥ የሚገቡ ይሆናል፤
 
 
•ከጉባኤው ርዕሰ ጉዳይ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ሲኖራቸው፣
•የተዘጋጁት የጥናት ጽሑፎች በፖሊሲ አውጭዎችና ፈፃሚዎች ጥቅም ላይ ሊውሉ እንደሚችሉ ሲታመንበት፣
•የጥናት ጽሑፎቹ ጥራት፣ አቀራረብና ያስቀመጡት የመፍትሄ ሃሳብ ወይንም አስተያየት፣
•ከቅጅ ነፃ መሆናቸው፡፡ 
አድራሻ
•ካሳሁን አድጐልኝ ስ.ቁጥር 0911-167802 E-mail፡ kassahunbelay77@yahoo.com
•ሚሊዮን ታደገ   ስ.ቁጥር 0911-549429  E-mail: milliontadege78@gmail.com
•አውግቸው ሰሙ   ስ.ቁጥር 0912-373873  E-mail፡ awgichews@gmail.com
በአካል ለማቅረብ ለምትፈልጉ ፋና ሕንፃ 4ኛ ፎቅ የሴክተር ልማት፣ ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት፡፡
ወሳኝ የጊዜ ሰሌዳ
•የጥናት ጽሑፍ አጽሕሮት ማቅረቢያ ቀን የሚጠናቀቀው ሚያዚያ 5 ቀን 2009 ዓ.ም.
•የውድድር አሸናፊዎች የሚገለጽበት ቀን ሚያዚያ 10 ቀን 2009 ዓ.ም.
•የጥናት ጽሑፎች የፓወር ፖይንት ስራ የሚገባበት የመጨረሻ ቀን ሚያዚያ 14 ቀን  2009 ዓ.ም.
 

Date: 
Fri, 03/31/2017
Image: 
Place: 
Bahir Dar University
Share