የመጽሐፍ ግምገማ ተካሄደ

ጥበበ  ሂስ
የመጽሐፍ ግምገማ ተካሄደ
 
በዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝ ተጽፎ ለንባብ በበቃው “አለመኖር” በተሰኘው ረዥም ልቦለድ መጽሐፍ ላይ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ምሁራዊ ሂስና ውይይት  ተካሔደ፡፡

የአቋማተ ዳይሬክተር አቶ መለሰ ገላነህ  በመርሃግብሩ መክፈቻ ላይ “አለመኖር”  አዲስ በመሆኑ ወይም ሽፋኑ ስላማረ ሳይሆን በውስጡ በያዘው ሀሳብና መልዕክት መሰረት ምሁራዊ ሂስ እንዲሰጥበት በተቋሙ የተመረጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

ልቦለዱን ዶ/ር አንተነህ አወቀ ከስነጽሁፍ እንዲሁም አቶ ታምሩ ደለለኝ ከስነልቦና አንፃር የገመገሙት ሲሆን በተጨማሪም ታዋቂው የፍልስፍና ምሁር ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በፍልስፍና መነፅር ቃኝተውታል፡፡

 
በመጨረሻም ዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝ በበኩሉ ስለመጽሐፉ አጠቃላይ አስተያየት እንዲሁም ከገምጋሚዎች እና ከተሳታፊዎች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ግምገማው ልቦለዱን ከስነጽሁፍ፣ከስነልቦና እና ከፍልስፍና አንፃር ያለውን ፋይዳ የቃኘ ሲሆን ከፍተኛ ውይይትና ገንቢ ሀሳቦች የተገኙበት ሲሆን መሰል የግምገማ መድረኮች በቀጣይ እንደሚዘጋጁ  አቶ መለሰ  ገልጸዋል፡፡

በስነሥርዓቱ የዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ተማሪዎች፣የተቋሙ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ደራሲዎችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

Share