News

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2007 ዓ.ም በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጭ የተሰሩና በወጥ የአማርኛ ቋንቋ አጠቃቀማቸውና ኢትዮጵያዊ የሆነውን ባሕል በማንፀባረቅ ለአማርኛ ቋንቋ እድገት የበኩላቸውን የተወጡ የፊልም ባለሙያዎችንና የፊልም ሥራዎችን በዩኒቨርሲቲው የቋንቋ ምሁራንና በታዋቂ የፊልም ባለሙያዎች አስገምግሞ በአሸናፊነት የተመረጡ ፊልሞችን በመሸለም እውቅና ሰጠ።
ታዋቂው የፊልም ስራና የማስታወቂያ ባለሙያ አርቲስት ተስፋየ ማሞ ለውድድር ስለቀረቡት 5 ፊልሞች ያላቸውን አጠቃላይ አስተያየት ገልፀዋል።
ፊልሞቹ በምስል፣ድምፅ፣ የትረካ ዘዴ፣ መብራት መሰረት ተገምግመው "የብራና መንገድ" የተሰኘው የደምስ አያሌው ፊልም 1ኛ በመሆን አሸንፏል።የፊልሙ አዘጋጅም የተዘጋጀለትን ሽልማት... Read More

የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም (አቋማተ) በዋግህምራ ዞን ሰቆጣ ከተማ ላቋቋመው ለአማርኛ ቋንቋ መምህራን ክበብ አባላት የ2 ቀን ስልጠና ሰጠ፡፡
ስልጠናው ሥነጽሑፍን ለአማርኛ ቋንቋ ማስተማሪያነት እንዴት መጠቀም እንደሚቻል፣ የአማርኛ ቋንቋ አብይና ንዑሳን ክሂሎችን ምን ምን እንደሆኑ፣ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የማስተማሪያ ሥነዘዴዎችን፣ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት አመታዊ፣ ዕለታዊና የምዕራፍ እቅዶች አዘገጃጀት እና የተለያዩ የስነልሳናዊ እሳቤዎችን በተመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ የቀረበ ነበር፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕ ጽ/ቤት ከሂዩማኒቲስ ፋካሊቲ ጋር በመተባበር ግንቦት 06/2007 ዓ.ም በደብረታቦር ከተማ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ክበብ መሰረተ፡፡