የጥናታዊ ፅሑፍ ጥሪ

በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልፀጊያ ተቋም (አቋማተ) በየስድስት ወሩ በሚያዘጋጀው ‘ርካብ’ በተሰኘ የአማርኛ ቋንቋ የምርምር መፅሔት በአማርኛ ቋንቋ የተፃፉ የምርምር ፅሑፎችን፤ ፍልስፍናዎችን፤ የመፅሐፍ ግምገማዎችን፤ ለውይይት የሚጋብዙ ፅሑፎችን እንዲሁም የስነፅሑፍና የስነጥበብ ስራ ማስተዋወቂያ/ማስገንዘቢያ ፅሁፎችን ማሳተም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከላይ በተጠቀሱት ዘርፎች ዙሪያ የተዘጋጁ ስራዎች ያሏችሁ ተመራማሪዎች ስራዎቻችሁን እንድትልኩ እንጋብዛለን፡፡ግንዛቤ ያህልም ከዚህ በታች የቀረቡ ነጥቦችን ይመልከቱ፡፡

¢የሚላኩ ስራዎች የተዘጋጁበት ቋንቋ፡- አማርኛ

¢የሚያተኩሩባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ወይም ይዘቶች፤

Øየአማርኛ ቋንቋ እድገት ከየት ወደ የት

Øየአማርኛ ቋንቋ በኢትዮጵያ ማህበራዊ፤ ምጣኔ ሃብታዊና ፖለቲካዊ ጉዞ ውስጥ የተጫወተው   ሚና፤

Øየአማርኛ ቋንቋ ስነልሳን ትንታኔ፤

Øየአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በኢትዮጵያ

Øአማርኛ እንሁለተኛ ቋንቋ (በመደበኛ ትምህርት)፤

Øመደበኛ አማርኛና የአማርኛ ዘዬዎች

Øየአማርኛ ቋንቋ ኢትዮጵያ ስነፅሑፍ እድገት ያበረከተው ድርሻ፤

Øአማርኛ ቋንቋና ስነጥበብ፤

Øአማርኛ ቋንቋና ባሕል፤

Øየአማርኛ ቋንቋ አጠቃቀም በመገናኛ ብዙሃን፤

Øየአማርኛ ቋንቋ አጠቃቀም በዘፈኖች፤በመዝሙሮችና በሙዚቃዎች፤

Øአማርኛ ቋንቋ ከኢትዮጵያ ውጭ፤

Øየግሰቦች፤የንግድ ድርጅቶችና የተቋማት የአማርኛ ስያሜዎች ከቋንቋው አጠቃቀም አንፃር ያላቸው አንድምታ፤

Øየአማርኛ ቋንቋ የወቅቱን የሳይንስና ቴክኖሎጅ ግኝቶች መግፅ አቅም፤

Ø  በማንኛውም የትምህርት መስክ (በታሪክ፣ በጂኦግራፊ፣ በባዮሎጂ፣ በኬሚስትሪ፣

 በፊዚክስ፣ በሒሳብ፤ በንግድ ስራ አስተዳደር፣ በሰው ሃብት አመራር፣ በሕግ፣ በመሬት

     አስተዳደር፣ ወዘተ.) በአማርኛ ቋንቋ የተሰሩ የምርምር ስራዎች፡፡

የስራው አቀራረብ

¢ ከ100-150 ቃላት የተዘጋጀ አፅሕሮተ ፅሑፍን (Abstract) ያካተተ ሰራ መሆን አበት፡፡

¢ ምርምር መፅሄት (Journal) ተገቢ በሚሆን መጠንና አቀራረብ የተዘጋጀ ፅሑፍ መሆን ይኖርበታል፡፡

¢ ስራው በ ‘Power Geez Unicode-1’ ተዘጋጅቶ በ ‘Word’ እና በ ‘PDF’ ተሰርቶ ይላካል፡፡

¢ ስራዎችን የመላኪያ ጊዜ፡- እስከ ጥቅምት 30/2008 ዓ.ም.

¢ የሚላክበት ኢሜይል:- rikabjournal@gmail.com

¢ የጥናታዊ ፅሑፉን አቀራረብ ዝርዝር መመሪያ ማግኘት ድረገፃችንን፡- http://bdu.edu.et/aldi/

    ይጎብኙ፡፡፡

ለበለጠማብራሪያ0911335298 ወይም 0583202013 ውሉወይምበመፅሄቱኢሜይል (rikabjournal@gmail.com ) ይፃፉ፡፡

Date: 
Fri, 10/02/2015
Image: 
Place: 
Bahir Dar University
Share