በደብረታቦር ከተማ አቡጊዳ የንባብ ማዕከል ለመገንባት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡

የዩኒቨርሲቲው የአማርኛ ቋንቋ ማበልፀጊያ ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር ሂሩት ካሳው የፕሮጀክቱን ዋና ዓላማ አስመልክቶ እንደተናገሩት ማዕከሉ የአካባቢውን ወጣቶች፣ ተማሪዎች፣ አዛውንቶች በንባብ ለማልማት የሚያስችሉ የተለያዩ መርሃግብሮች ማለትም እንደ ስነፅሁፍ ምሽት፣ የንባብ ቀን፣ የቅኔና የስነቃል፣ የመሪዎች ወግ፣ የአዛውንቶች ወግ እንዲሁም ሌሎች ነገሮች ሣምንታዊ፣ወርሃዊና ዓመታዊ ፕሮግራሞች የሚከናወኑበት ምቹና አረንጓዴ ማዕከል እንደሚሆን አስገንዝበዋል፡፡
ዶ/ር ሂሩት አክለውም ማዕከሉ ለዩኒቨርሲቲው የአማርኛ ቋንቋ ተመራማሪዎችና መምህራን የሚገለገሉበትና የተለያዩ ችግር ፈች ምርምሮች የሚያካሂዱበት እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
በዕለቱ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባና የትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ደሳለኝ አቤ፣ አቶ አዳነ ጌታነህ የከተማው ኢንዱስትሪና ከተማ አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ በጋራ የማዕከሉን መገንቢያ  የቦታ ካርታ ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተወካይ አቶ አድማሱ ፈንታ፣ ዶ/ር ሂሩት ካሳው እና ዶ/ር ስዩም ተሾመ አስረክበዋል፡፡
በርክክቡ ወቅት በቦታው የተገኙት የወረዳው አመራር አካላት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለይ በአማርኛ ቋንቋ ማበልፀግ ዙሪያ መልካም ተሞክሮዎችን እያበረከተ መሆኑን ገልፀው ይህን ስራ ለመደገፍም የከተማው አስተዳደር በአጭር ጊዜ ውስጥ 15,000 ካ.ሜ የሚሸፍን 15,000 ካ.ሜ የሚሸፍን ቦታ በመስጠት ለአማርኛ ቋንቋ መበልፀግ አጋርነቱን ማሳየቱ እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል፡፡

 

Share