በተቋሙ የሚከናወኑ ተግባራት

 

ተቋሙ የሚከናወኑ ተግባራት፡-

የተቋሙን ዓላማ ከግብ ለማድረስ በተቋሙ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፡፡ 

    ·   የቋንቋውን መድብለ ቃላት መሰብሰብና መሰነድ፤

·      አዳዲስ ጽንሰ ሃሳቦች አቻ የሆኑ የአማርኛ ስያሜ መስጠትና ማላመድ፤

·      የአማርኛ ዘዬዎች በአይነታቸውና በተነፃፃሪ እንዲሰነዱ ማድረግ፤

·      የቋንቋው ሆህያት የቋንቋውን ስርዓተ ጽሕፈትና መድብለ ቃላት በሚያሳድጉበት ሁኔታ ላይ መስራት፣ እንዲሁም ሆህያቱ በትክክለኛ ቅርጻቸው ወጥ የሆነ አጠቃቀም እንዲኖራቸው የማላመድ ስራ መስራት፤

·      መማሪያና ማስተማሪያ መፃህፍትን በመገምገም ጉድለቶችን በማሟላትና ስህተቶችን በማረም የቋንቋ ትምህርቱ በተገቢው መንገድ እንዲሰጥ ማገዝ፤

·      በውጭ ቋንቋዎች የተዘጋጁ ጽሁፎችን/ሰነዶችን፣ ማሰልጠኛ መምሪያዎችን፣ወዘተ. ወደአማርኛ ቋንቋ በመመለስ/ መተርጎም የቋንቋውን እድገት ማገዝ፤

·      በጽሁፍ ታትመው የሚወጡ የህትመት ውጤቶችን፣ ማስታወቂያዎችን…  በመገምገም ማስተካከያ በመስጠት እገዛ ማድረግ፤

·      የንባብ ማዕከላትን በማቋቋም የንባብ ባህልን መፍጠር፤

·      ከመገናኛ ብዙሃንና ከትምህርት ቤቶች ጋር አብሮ በመስራት መደበኛው የቋንቋ አጠቃቀም እንዲዳብር ማድረግ፤

·      የቋንቋውን ታሪክ መፃፍ፤ለህትመት ማብቃት፤

·      ለፖሊሲ አውጭዎች የምርምር ውጤቶችን መሰረት በማድረግ የማማከር ድጋፍ መስጠት፤

·      በቋንቋው የተፃፉ የንባብ፣ የማስተማሪያና የመማሪያ መጽሐፎችን መሰብሰብና መሰነድ፤

·         በአማርኛ ቋንቋና በመማር ማስተማሩ ዙሪያ የተደረጉ ምርምሮችና ግኝታቸውን መቃኘትና ጠቃሚዎቹ ተግባራዊ የሚሆኑበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤ መፍጠር፡፡

ማህበረሰቡ ለቋንቋው አዎንታዊ ግንዛቤ እንዲኖረው ግንዛቤ መፍጠር፤

Share